አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ ከአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ጉዳይ ረዳት ሚኒስትር ሞሊ ፊ ጋር ተወያዩ

You are currently viewing አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ ከአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ጉዳይ ረዳት ሚኒስትር ሞሊ ፊ ጋር ተወያዩ

AMN – መስከረም 15/2017 ዓ.ም

በኒውዮርክ እየተካሄደ ከሚገኘው 79ኛው የተ.መ.ድ ጠቅላላ ጉባዔ ጎን ለጎን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ ከአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ጉዳይ ረዳት ሚኒስትር ሞሊ ፊ ጋር የጋራ ትኩረት በሚሹ ጉዳዮች ዙሪያ ተወያይተዋል።

ሚኒስትሩ በኢትዮጵያ እና አሜሪካ መካከል ጠንካራ ግንኙነት መኖሩን በመግለጽ በቀጣይ የጋራ ትኩረት በሚሹ ጉዳዮች ዙሪያ ቀጣይነት ያለው ውይይት አስፈላጊ መሆኑን አንስተዋል።

አምባሳደር ታዬ ለረዳት ሚኒስትሯ በአፍሪካ ቀንድ ወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ገለጻ ባደረጉበት ወቅት በተለይ ኢትዮጵያ በቀጣናው ዘላቂ ሰላም እና መረጋጋት እንዲሰፍን እያደረገች ያለውን ጥረት ትኩረት ሰጥተው አንስተዋል።

ሚኒስትሩ ሶማሊያን በተመለከተ ከሞሊ ፊ ጋር በነበራቸው ውይይት ኢትዮጵያ ሽብርተኞችን በመዋጋት ረገድ በምታደርገውን የተጠናከረ ጥረት ዙሪያ ገለጻ አድርገዋል።

የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት ሚኒስትር ሞሊ ፊ በበኩላቸው አሜሪካ ሽብርተኝነትን በመዋጋት እና አጠቃላይ በቀጣናው ሰላም እና መረጋጋት ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ትብብር አጠናክራ እንደምትቀጥል ማረጋገጣቸውንም ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

#Addisababa

#Ethiopia

ትክክለኛውን የአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ዲጂታል ሚዲያ የትስስር አውታሮችን በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑን!

https://linktr.ee/AddisMediaNetwork

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review