AMN – መስከረም 27/2017 ዓ.ም
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እና የፌዴሬሽን ምክር ቤት አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴን ለኢፌዴሪ ፕሬዚዳንትነት ሰይመዋል።
አዲሱ ፕሬዚዳንት በሁለቱ ምክር ቤቶች ፊት ቀርበው ቃለ-መሐላ የፈፀሙ ሲሆን የቀድሞዋ የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ ኃላፊነቱን አስረክበዋቸዋል።
6ኛው የኢፌዲሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እና የፌዴሬሽን ምክር ቤት 4ኛ ዓመት የሥራ ዘመን መክፈቻ ሥነ-ሥርዓት እየተካሄደ ይገኛል።
በዮናስ በድሉ