አራዳ ሌግዤሪ ሞል በፍጥነትና ጥራት እየተከናወነ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ተናገሩ

You are currently viewing አራዳ ሌግዤሪ ሞል በፍጥነትና ጥራት እየተከናወነ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ተናገሩ

AMN- ሰኔ 10/2017 ዓ.ም

አዲስ አበባ ከተማን ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪ የሚያደርገው እና በኢትዮጵያ የመጀመሪያ የሆነው አራዳ ሌግዤሪ ሞል፣ በፍጥነትና ጥራት እየተከናወነ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ተናግረዋል፡፡

የፕሮጀክቱን ሂደት በስፍራው ተገኝተው የጎበኙት ከንቲባ አዳነች አቤቤ፣ ፕሮጀክቱ የመዲናዋን ገጽታ ከማጎላቱ ባሻገር፣ የንግድና የመዝናኛ ማእከል የማድረግ ትልምን የሚያሳካ ነው ብለዋል፡፡

ለዓመታት በተገቢው ሁኔታ ትኩረትን ሳታገኝ የኖረችው አዲስ አበባ፣ ያላት ስምና የከታማዋ ደረጃ ሳይመጣጠኑ መቆየታቸውንም አንስተዋል፡፡

ስምና ግብሯ ይገጥሙ ዘንድ ከፍ ሲልም ለነዋሪዎቿ የተመቸች ውብ ከተማ እንድትሆን ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ በከተማዋ እየተሰሩ ያሉ ፕሮጀክቶች ህያው ምስክር ናቸው ሲሉም አብራርተዋል፡፡

ፕሮጀክቶቹ ገጽታን የመገንባትና ውበትን የመፍጠር ብቻ ሳይሆን፣ ዜጎች የተሻለ የአኗኗር ዘይቤን እንዲከተሉና የተሻለ ኑሮ እንዲኖሩ ለማስቻል መሆኑንም አንስተዋል፡፡

አራዳ ሌግዤሪ ሞል ፕሮጀክት ከተማዋ የገቢ አቅሟን የምታሳድግበት ሲሆን በተጀመረ ሰባት ወራት ውስጥም በፍጥነትና ጥራት እየተከናወነ እንደሚገኝ ገልጸዋል፡፡

ፕሮጀክቱ በመንግስትና በግል አጋርነት በጋራ እየተገነባ የሚገኝ መሆኑን ያነሱት ከንቲባዋ፣ ግንባታው ከወንዝ ዳርቻ ልማት አንዲሁም ሌሎች ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ካለቸው የልማት ስራዎች ጋር የተሰናሰለ ስለመሆኑም አንስተዋል፡፡

በአንዋር አህመድ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review