አቅመ ደካማ ዜጎች ከተረጂነት ወደ ምርታማነት እንዲሸጋገሩ ለማድረግ የተጀመረው ከተማ አቀፍ ጥረት ተጠናክሮ ይቀጥላል-የአዲስ አበባ ከተማ የስራና ክህሎት ቢሮ

You are currently viewing አቅመ ደካማ ዜጎች ከተረጂነት ወደ ምርታማነት እንዲሸጋገሩ ለማድረግ የተጀመረው ከተማ አቀፍ ጥረት ተጠናክሮ ይቀጥላል-የአዲስ አበባ ከተማ የስራና ክህሎት ቢሮ

AMN – ታኅሣሥ 27/2017 ዓ.ም

በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኙ አቅመ ደካማ ዜጎች ከተረጂነት ወደ ምርታማነት እንዲሸጋገሩ ለማድረግ የተጀመረው ከተማ አቀፍ ጥረት ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የአዲስ አበባ ከተማ የስራና ክህሎት ቢሮ አስታወቀ፡፡

በምግብ ዋስትና ሴፍቲኔት ፕሮግራም የስራ እድል አግኝተው ሲሰሩ የነበሩ ከተረጂነት ወደ አምራችነት የተሸጋገሩ 31ሺ 2 የከተማዋን ነዋሪዎች ከንቲባ አዳነች አቤቤ በተገኙበት ተመርቀዋል፡፡

በመርሐግብሩ ላይ በምክትል ከንቲባ ማእረግ የአዲስ አበባ ከተማ ስራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ አቶ ጥራቱ በየነ እንደገለጹት፣ በመጀመሪያ ዙር የምግብ ዋስትና ማረጋገጥ መርሃግብር ከ415 ሺ በላይ የከተማዋ ነዋሪዎች ተጠቃሚ ሆነዋል፡፡

ከ2014 ዓ.ም ጀምሮ አቅመ ደካማ እንዲሁም ክህሎትና ድጋፍ ከተሰጣቸው ራሳቸውን መመገብና ቤተሰባቸውን ማገዝ የሚችሉ ከ216 ሺ በላይ የአዲስ አበባ ነዋሪዎችን ተጠቃሚ ለማድረግ በሁለተኛ ዙር ስልጠና ሲሰጥ መቆየቱንም አስታውቀዋል፡፡

በዚሁ ዙር የምግብ ዋስትና ሽግግር የተመሩ ተመራቂዎችን በቆሻሻ አወጋገድ፣ በውበትና አረንጓዴ ልማት በመሳሰሉ የአካባቢ ጥበቃ አነስተኛ የመሰረተ ልማት ግንባታ እንዲሁም በከተማ ግብርና ስራዎች ላይ በመሳተፍ ለከተማዋ በጎ ገጽታ የድርሻቸውን ሲወጡ የቆዩ መሆናቸውንም አቶ ጥራቱ ገልጸዋል፡፡

ለነዚሁ ሰልጣኝ ምግብ ዋስትና ተመራቂዎች አጠቃላይ 1.3 ቢሊዬን ብር ድጋፍ ስለመደረጉ ያስታወቁት አቶ ጥራቱ ተመራቂዎቹ በመረጡት የሙያና ስራ ዘርፍ የስራ ዕድል እንዲፈጠርላቸው ተደርጓልም ብለዋል፡፡

ይህንን በማጠናከር በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ለሚገኙ ዜጎች የፍትሃዊ ተጠቃሚነትን ማሳደግ የሚያችል አዲስ ፕሮጀክት በከተማ ደረጃ ይፋ እንደሚደረግም አስታውቀዋል፡፡

የ2ኛ ምዕራፍ የከተማ ልማትና ምግብ ዋስትና የተሸጋገሩ ተመራቂዎችም የወሰዱት በተግባር በስራ የተፈተነ ስልጠና ከነበሩበት ህይወት የሚያወጣና ራሳቸውንም ቤተሰባቸውንም የሚቀይር ስለመሆኑ አንስተዋል፡፡

በአቡ ቻሌ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review