አትሌት ሸላቃ ኃይሌ ገ/ስላሴ የኦሜድላ ስፖርት ክለብ የቦርድ ሰብሳቢ ሆነ

You are currently viewing አትሌት ሸላቃ ኃይሌ ገ/ስላሴ የኦሜድላ ስፖርት ክለብ የቦርድ ሰብሳቢ ሆነ

የኦሜድላ ስፖርት ክለብ ቦርድ በአዲስ መልክ የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ዴኤታና ታዋቂ ስፖርተኞች በተገኙበት በአዲስ አበባ በአዲስ መልክ ተመሰርቷል።

በዚህም አትሌት ሸላቃ ኃይሌ ገ/ስላሴ የኦሜድላ ስፖርት ክለብ የቦርድ ሰብሳቢ ሆነ ተመርጧል። ወርቃማውን የኦሜድላ ስፖርት ክለብ ዓርማና የክለቡ አደረጃጀት መመሪያ ሰነድ ከፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል እጅ ተቀብሏል።

የተሰጣቸው ኃላፊነት ከባድ መሆኑንና የኦሞድላ ስፖርት ክለብ ወደ ነበረበት ለመመለስ የሁሉንም ድጋፍና ርብርብ እንደሚያስፈልግም ገልፀዋል።

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጄኔራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል፣ እንደ ኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ሁሉም የሥራ ዘርፎች በባለሙያ ሲመሩ ውጤት እንዳመጡ ተመልክተናል፤ ኦሜድላ ስፖርት ክለብም በባለቤቶቹ ከተመራና የተቋሙ የበላይ አመራር እገዛ ክለቡ ገለልተኛ ሆኖ ከተመራ ወደ ነበረው ዝናና ክብሩ የሚመለስበት ቀን ሩቅ አይሆንም ብለዋል።

ቦርዱን በአዲስ መልክ አቋቁመን አጠናክረን በመምራት እንደትላቱ አትሌቶችን ከሠራዊቱ እያፈራን ኢትዮጵያን በአለም ደረጃ የሚያስተዋውቅና ስሟን የሚያስጠሩ ስፖርተኞች የሚናፈራበት ክለብ ይሆናል ብለዋል።

የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ዴኤታአምባሰደር መስፍን ቸርነት በቦርድ ምስረታው ላይ በኢትዮጵያ የስፖርት ታሪክ ውስጥ ትልቅ አሻራ ጥሎ ያለፈው ኦሜድላ የስፖርት ክለብ ከነበረበት ወርቃማ ጉዞ ወርዶ እንደገና ለማንሰራራት በሚያደርገው የጉዞ ሂደት የተቋሙ አመራሮች ኦሜድላ የስፖርት ክለብ ቀድሞ የነበረውን ታሪክ ለመመለስ በቁጭት ተነሳስታችሁ ስትራቴጂክ ውሳኔ ወስናችሁ ክለቡ ወደ ፊት የሚሄድበትን ትልቅ ውሳኔ ወስናችኋል ብለዋል።

የኦሜድላ ስፖርት ክለብ ታሪክ ሰሪ ጀግኖች ያሉበትና አንጋፋ ስፖርተኞች ያፈራ ትልቅ ልምድ ያለው በመሆኑ በአለም አቀፍ የስፖርት መድረኮች ላይ የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማን ከፍ አድርገው የሚያውለበልቡ ስፖርተኞችን በማፍራት ውጤታማ እንደሚሆን መግለፃቸውን ከኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review