አትሌት ትዕግስት አሰፋ በበርሊን ማራቶን የዓለም ክብረወሰን ሰበረች

You are currently viewing አትሌት ትዕግስት አሰፋ በበርሊን ማራቶን የዓለም ክብረወሰን ሰበረች

ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ትግስት አሰፋ ዛሬ በበርሊን ማራቶን አዲስ የአለም ክብረወሰን በማስመዝገብ አሸንፋለች።

የባለፈው አመት የበርሊን ማራቶን አሸናፊዋ አትሌት ትእግስት አሰፋ ርቀቱን 2 ሰአት ከ11 ደቂቃ ከ53 ሰከንድ በሆነ ሰአት በመሸፈን በአትሌት ብሪግድ ኮስጊ እጅ የነበረውን የአለም ክብረወሰን ከሁለት ደቂቃዎች በላይ አሻሽላለች ።

ኬንያዊቷ ኮስጊ እ ኤ አ በ2019 የቺካጎ ማራቶን 2 ሰአት ከ14 ደቂቃ ከ 04 ሰከንድ አዲስ የአለም ክብረወሰን አስመዝግባ እንደነበር ይታወሳል።

በውድድሩ ከአትሌት ትእግስት በተጨማሪ አምስት ኢትዮጵያኖች ከ4ኛ እስከ 10ኛ ባለው ደረጃ ውስጥ በመግባት አንጸባራቂ ውጤት አስመዝግበዋል።

በወንዶች ትልቅ ግምት አግኝቶ የነበረው ኬንያዊው ኤሉድ ኪፕ ቾጌ ቀዳሚ በመሆን አሸንፏል።

በውድድሩ ሌላው ኬንያዊ አትሌት ቪንሰንት ኪፕኬሞይ 2ኛ ሲወጣ ኢትዮጵያዊው አትሌት ታደሰ ታከለ ደግሞ 3ኛ ደረጃን ይዞ አጠናቋል።

በበላይነህ ይልማ

ትክክለኛውን የአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ዲጂታል ሚዲያ የትስስር አውታሮችን በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑን!

YouTube ➲ http://bit.ly/3itThRr

Telegram ➲ http://bit.ly/3W4puw9

Facebook ➲ https://bit.ly/3CJVgI8

Twitter ➲ http://bit.ly/3IKQ3TZ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review