አቶ ተመስገን ጥሩነህ ከቼክ ሪፐብሊክ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማሪያን ዩሬችካ ጋር ተወያዩ

AMN ኅዳር -30/2017 ዓ.ም

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ተመስገን ጥሩነህ ዛሬ ከቼክ ሪፐብሊክ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማሪያን ዩሬችካ ጋር በሁለትዮሽ ጉዳዮች ዙርያ መወያየታቸውን አስታወቁ፡፡

አቶ ተመስገን ጥሩነህ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው በርካታ ዓመታትን የዘለቀውን የኢትዮ-ቼክ ግንኙነትን ለማጠናከር በረጅም ጊዜ የብድር ስምምነት እና በልማት ትብብር ዙሪያ በጋራ ለመሥራት የመግባቢያ ሰነድ ተፈራርመናል ብለዋል፡፡

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማሪያን ዩሬችካ ኢትዮጵያ እያከናወነች ያለችውን የልማት እንቅስቃሴ ማድነቃቸውን ጠቁመዋል፡፡

በተለይም የቼክ መንግሥት በቱሪዝም እና በዱር እንስሳት ጥበቃ ዙርያ በትብብር ለመሥራት ፍላጎት እንዳለው ገልጸውልኛልም ብለዋል፡፡

በጋራ ጉዳዮች ዙሪያ የሁለቱ ሀገራት ትብብር ተጠናክሮ እንዲቀጥል ከስምምነት ላይ ደርሰናልም አው ያሉት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስተትር አቶ ተመስገን በመልእክታቸው፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review