አቶ አሕመድ ሽዴ ከዓለም አቀፍ የገንዘብ ትብብር ማኔጂንግ ዳይሬክተር እና ከባለብዙ ወገን ኢንቨስትመንት ዋስትና ኤጀንሲ ጋር ተወያዩ

You are currently viewing አቶ አሕመድ ሽዴ ከዓለም አቀፍ የገንዘብ ትብብር ማኔጂንግ ዳይሬክተር እና ከባለብዙ ወገን ኢንቨስትመንት ዋስትና ኤጀንሲ ጋር ተወያዩ

AMN – ጥቅምት 18/2017 ዓ.ም

የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አሕመድ ሽዴ ከዓለም አቀፍ የገንዘብ ትብብር ማኔጂንግ ዳይሬክተር ማክታሃር ዲዮፕ እና ከባለብዙ ወገን ኢንቨስትመንት ዋስትና ኤጀንሲ ምክትል ፕሬዚዳንት ኢትዮጲስ ተፈራ ጋር ተወያይተዋል፡፡

ሚኒስትሩ ውይይቱን ያካሄዱት ከዓለም ባንክ እና ከዓለም ዐቀፉ የገንዘብ ተቋም አመታዊ ስብሰባዎች ጎን ለጎን እንደሆነም ታውቋል፡፡

ውይይቱ በኢትዮጵያ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ እና ከግል ሴክተሮች ጋር በቅርበት መሥራት በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ እንዳተኮረም ተገልጿል።

ኢትዮጵያ የግሉን ዘርፍ በኢኮኖሚ ውስጥ ለማሳተፍ እያደረገች ያለው ጥረት በውይይቱ መነሳቱም ተገልጿል፡፡

እንደ ገንዘብ ሚኒስቴር መረጃ በቅርቡ ለዓለም አቀፍ ኢንቨስተሮች ምቹ ሁኔታን ለመፍጠር የተደረጉ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያዎች ገለጻ ተደርጓል፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review