AMN- ጥቅምት 6/2017 ዓ.ም
በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ኃላፊ እና የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አደም ፋራህ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት የኢትዮጵያ ኅብረት ሥራ ኮሚሽን ኮሚሽነር በነበሩት ጌታቸው መለሰ (ዶ/ር) ሕልፈተ ሕይወት የተሰማቸውን ሐዘን ገለጹ፡፡
አቶ አደም ለቤተሰቦቻቸው፣ ለወዳጅ ዘመዶቻቸው እና ለሥራ ባልደረቦቻቸው መጽናናትን ተመኝተዋል፡፡