አንድ ደላላ እና ሁለት ፈፃሚዎች በወንጀል ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር ዋሉ

You are currently viewing አንድ ደላላ እና ሁለት ፈፃሚዎች በወንጀል ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር ዋሉ

AMN – ጥቅምት 14/ 2017 ዓ.ም

በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 1 ሰልፍ በመያዝ እና ተገልጋይ በመመዝገብ ገንዘብ የሚሰበስብ በፓርኪንግ ስራ ላይ የተሰማራ ህገ-ወጥ ደላላ እና ከደላላ ጋር ተመሳጥሮ በሌብነት ላይ የተሰማራ አንድ የንግድ ቢሮ የወረዳ ጽ/ቤት ሰራተኛ እንዲሁም የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ጽ/ቤት ሰራተኛ በፖሊስ ቁጥጥር ስር እንዲውሉ ተደርጓል።

ለከተማ አሰተዳደሩ ከነዋሪ በደረሰ ጥቆማ መነሻ የኤጀንሲው ስነ-ምግባር እና ፀረ-ሙስና ዳይሬክቶሬት ከአዲስ አበባ ፖሊስ ጋር ባደረገው ክትትል ካድረጉት የስልክ የድምፅ ልውውጥ ጋር በኤግዚቢትነት በቁጥጥር ስር እንዲውሉ አድርጓል።

ፖሊስ ጉዳይ ላይ መረጃ በማሰባሰብ ምርመራ እያደረገ ያለ ሲሆን፤ ጥቆማውን ለሰጠው ነዋሪ ምስጋና ማቅረቡን ከከንቲባ ጽሕፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review