አካባቢን ማጽዳት ንፅህናን ከመጠበቅ ባለፈ አብሮነትን የሚያጎለብት ተግባር በመሆኑ ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል፡- ነዋሪዎች

You are currently viewing አካባቢን ማጽዳት ንፅህናን ከመጠበቅ ባለፈ አብሮነትን የሚያጎለብት ተግባር በመሆኑ ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል፡- ነዋሪዎች

AMN- መስከረም 10/2017 ዓ.ም

አካባቢን በማፅዳት ዙሪያ በጋራ የሚከናወኑ ተግባራት ላይ መሳተፍ የአካባቢን ንፅህና ከመጠበቅ ባለፈ አብሮነትን የሚያጎለብት ተግባር በመሆኑ ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ገልጸዋል፡፡

” የእኔ ቆሻሻ የሁላችንም ሀብት ፣ የመፍትሄው አካል ይሁን” በሚል መሪ ሀሳብ በአዲስ አበባ ለ4ኛ ጊዜ ዓለም አቀፍ የፅዳት ቀን ተከብሯል፡፡

በመርሀ ግብሩ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ ፅዳት አስተዳደር ኤጀንሲ እና የተባበሩት መንግስታት ሀቢታት( UN – HABITAT ) በጋራ በመሆን ከማለዳው 12 ሰዓት ጀምሮ ከተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎች ጋር በመሆን ዓለም አቀፍ የፅዳት ቀን ምክንያት በማድረግ በከተማዋ የፅዳት ዘመቻ አካሂደዋል፡፡

ፅዳት ከግለሰብ የሚጀምር ቢሆንም በማህበረሰቡ ውስጥ የሚካሄዱት ንቅናቄዎች ከተማን በማስዋብ እና በማፅዳት ሂደት ውስጥ ከፍተኛ አበርክቶ እንዳላቸው በቢሮ ኃላፊ ማዕረግ የአዲስ አበበ ከተማ ምክትል ዋና ስራ አስኪያጅ ተፈራ ሞላ ገልፀዋል፡፡

በሌላ በኩል በከተማዋ በተለያዩ ጊዜያት የሚካሄዱ የፅዳት ዘመቻዎች ከተማዋን የተሻለ ፅዱ እንድትሆን አድርጓል ያሉት ደግሞ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የተባበሩት መንግስታት ሀቢታት ( UN – HABITAT ) ኢትዮጵያ ካንትሪ ፕሮግራም ዳይሬክተር ሀረገወይን በቀለ ናቸው፡፡

የአዲስ አበበ ከተማ ፅዳት አስተዳደር ኤጀንሲ የጥናት ፕሮጀክት ትግበራ ዳይሬክቶሬት ተወካይ ራሄል አስራት በበኩላቸው በመላው ዓለም ሀገራት የሚከበረው ዓለም አቀፍ የፅዳት ቀን በዓለም ያለውን 5 በመቶ ሕዝብ በፅዳት ዘመቻ የማሳተፍ ዓላማን የያዘ መሆኑን አንስተዋል፡፡

በመርሃ ግብሩ አካባቢዎቻችንን ለማጽዳት ሕግ እና ስርዓት እስኪወጣ እና ቅጣት እስኪተላለፍብን መጠበቅ የለብንም በጋራ በመሆን የከተማችንን ፅዳት መጠበቅ አለብን ብለዋል የጽዳት ዘመቻው ተሳታፊዎቹ።

ዓለም አቀፍ የፅዳት ቀን በተቀናጀ መልኩ መካሄዱም ተነግሯል፡፡

በዳንኤል መላኩ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review