አዋሽ ባንክ “ለላቀ የደንበኞች አገልግሎት እንተጋለን” በሚል መሪ ሀሳብ የደንበኞች ሳምንትን እያከበረ ነው

You are currently viewing አዋሽ ባንክ “ለላቀ የደንበኞች አገልግሎት እንተጋለን” በሚል መሪ ሀሳብ የደንበኞች ሳምንትን እያከበረ ነው

AMN – የካቲት 10/2017 ዓ.ም

በፕሮግራሙ ላይ የአዋሽ ባንክ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ፀሐይ ሽፈራው በዛሬው ዕለት በዋና መስሪያ ቤት እና በሁሉም ቅርንጫፎች መርሃ ግብሩ እየተካሄደ መሆኑን ገልፀዋል።

መርሀግብሩ ከዛሬ ጀምሮ ለአንድ ሳምንት የሚቆይ ሲሆን፣ የደንበኞችን ፍላጎት ማርካት እና የአገልግሎት ጥራት ለመጨመር ታስቦ የሚከናወን መሆኑን አንስተዋል።

ባንኩ ለህብረተሰቡ የሚሰጠውን አገልግሎት ለማሻሻል ሁሌም እንደሚሰራ ገልፀዋል።

ባንኩ ደንበኞች የተሟላ አገልገሎት እንዲያገኙ እየሰራ ይገኛል ያሉት ዋና ስራ አስፈፃሚው፣ የዲጂታል ፋይናንሽያል አገልግሎቱን ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ እየተሰራ እንደሚገኝ ተናግረዋል።

ደንበኞች በቀላሉ የተለያዩ ክፍያዎችን እንዲፈፅሙ የባንኩን ዲጂታል ባንኪንግ አገልግሎት የማዘመን ስራ እየተሰራ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡

እንዲሁም “የደንበኞቻችንን ፍላጎት በዲጂታል ባንኪንግ ለማርካት እንተጋለን” በሚል መሪ ሀሳብ ከየካቲት 10 እስከ 17 ቀን 2017 ዓ.ም ለአንድ ሳምንት የሚቆይ የዲጂታል ወርም በዛሬው ዕለት ይፋ መደረጉን ዋና ስራ አስፈፃሚው አስታውቀዋል።

አዋሽ ባንክ ላለፉት 30 ዓመታት ዘመናዊ እና አስተማማኝ የባንክ አገልግሎትን በመስጠት በአሁኑ ጊዜ በመላው ሀገሪቱ ተደራሽነቱን በማስፋት ከ983 በላይ ቅርንጫፎች ያሉት ሲሆን፣ ከ14 ሚሊየን በላይ ደንበኞችን ማፍራቱም ተገልጿል፡፡

በመሀመድኑር አሊ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review