AMN – ታኅሣሥ 26/2017 ዓ.ም
• ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ማዕድ ማጋራት ተደጋግሞ እየተደረገ፣ ባህልም እየሆነ መጥቷል፡፡ ለመሆኑ የዚህ የመጠያየቅና የመደጋገፍ ባህል አንድምታ እንዴት ይታያል? የበለጠ እንዲጎለብትስ ከማን ምን ይጠበቃል? ስትል ምሁር ጠይቃ ዘገባ አጠናቅራለች፤
• ከሶስት ዓመታት እድሳ በኋላ ለጉብኝት ክፍት የሆነው ብሔራዊ ቤተ መንግስት የአብሮነታችን ገመድ የበለጠ እንዲጠነክር በማድረግ ረገድ ስላለው ፋይዳ ምሁራንን ጠይቃ ያገኘችውን እንካችሁ ትላለች፤
• የቀድሞው የአፍሪካ አንድነት ድርጅት፣ የአሁኑ የአፍሪካ ህብረት ምስረታና እስካሁን ባለው ጉዞው ኢትዮጵያ ያላትን አይተኬ ሚና በመፈተሽ የዚህን አንድምታ ታስዳስሳለች፤
• በለነገዋ የሴቶች ተሃድሶና ክህሎት ማበልፀጊያ ማዕከል በልብስ ስፌት ሙያ በመሰልጠን ወደ ስራው ዓለም ስለገባች ወጣት የህይወት ውጣ ውረድ እና አሁን ስለሰነቀችው ብሩህ ተስፋ በጥቅሉ ኑረቷን ቃኝታለች፤ እናንተንም ታስቃኛለች፤
• ከራሳቸው ፍጆታ አልፈው ለሌሎች ምርታቸውን መሸጥ የጀመሩ ሰዎችን ተሞክሮ መነሻ በማድረግ የሌማት ትሩፋት በበዓል ሰሞን ያለው የፍጆታ ግብዓት ከፍ እንዲል እያሳደረ ያለውን አወንታዊ ተፅዕኖ ታስቃኛችኋለች
የመዝናኛ እና ስፖርት እንዲሁም ልጆችን ታሳቢ ያደረጉ ጉዳዮችን ጨምሮ አንብበው የሚማሩባቸውንና የሚዝናኑባቸውን ዘገባዎች ከማስታወቂያዎች ጋር ይዛ ወጥታለች። ጋዜጣችንን ማከፋፈልም ሆነ ቋሚ አንባቢ ለመሆን 5 ኪሎ ከማህበረ ቅዱሳን ህንፃ ዝቅ ብሎ ወደሚገኘው አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ይምጡ።