አዲስ ልሳን ጋዜጣ በውብ ገፅታና በአዲስ አቀራረብ የተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮችን በመያዝ ዘወትር ቅዳሜ ከእጃችሁ መድረሷን ቀጥላለች፡፡ በዛሬ እትሟ፡-
በዜና አምድ
• የብልፅግና ፓርቲ 2ኛ መደበኛ ጉባኤን የተመለከቱ ጉዳዮችን ሰፊ ሽፋን ሰጥታለች፤
• የአፍሪካን ችግሮች በአህጉር በቀል መፍትሄዎች ለመፍታት ምን ይደረግ? ስትል ፈትሻለች፤
አንኳር ጉዳይ
• የብልፅግና አባላት በአዲስ አበባ የተለያዩ ስፍራዎች ያደረጉት ጉብኝትና የሰጡት አስተያየትን አጠናቅራ ይዛለች፤
• በተጨማሪም የፓርቲ ጉባኤው በሀገር መጻኢ እድል ላይ የሚኖረው አበርክቶ እስከምን ድረስ ነው? ስትል ጠይቃለች፤
ከህዝብ አንደበት
• የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ከብልፅግና ጉባኤ ምን ይጠብቃሉ ስትል ተዘዋውራ ጠይቃ ቃኝታለች፤
በህይወት መንገድ
• የጂኦ ቱሪዝም ባለሙያ ለመሆን የተደረገ የህይወት ጉዞን ዳስሳለች፤
የጠዋት ፀሐይ
• በመዲናዋ የተገነቡ አዳዲስ የልጆች የመዝናኛ ስፍራዎች ስፍራዎችን እያዋዛች ትጠቁማለች፤
መዝናኛ
• የአዲስ አበባ የባለፉት አመታት የኪነ ጥበብ እንቅስቀሴ ዳናን እየተከተለች ዳሰሳ አድርጋለች፤
• እንዲሁም በሳምንቱ መጨረሻ ቀናት ተዝናኖትን ሊፈጥሩልዎ የሚችሉ የጥበብ ድግሶች ጥቆማን ይዛለች
ስፖርት
• ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በስፋት እየተዘወተረ ስለመጣው ማስ ስፖርት ሰፋ ያለ ዘገባንም ይዛለች
በተጨማሪም ጤና፣ ኢኮኖሚ፣ ህግ፣ የፎቶ ዘገባ እና ሌሎችም ጉዳዮች በጥልቅ ትንታኔ፣ በውብ አቀራረብና በሳቢ ገፅታ ተሰናድተው እነሆ! ትላለች፡፡
መልካም ንባብ
አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ አዲስ ልሳን ጋዜጣ፤ የትውልድ ድምፅ!