አዲስ ሚዲያ ኔትወርክ በአገልግሎት አሰጣጥ ላይ የሚስተዋሉ ጉድለቶችን ነቅሶ በማውጣት የማስተካከያ እርምጃ እንዲወሰድ የጎላ ሚና ተጫውቷል- የፐብሊክ ሰርቪስ እና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ

AMN- ጥር 15/2017 ዓ.ም

አዲስ ሚዲያ ኔትወርክ በአገልግሎት ዘርፉ የሚስተዋሉ ጉድለቶችን ነቅሶ በማውጣት የማስተካከያ እርምጃ እንዲወሰድ የጎላ ሚና መወጣቱን የፐብሊክ ሰርቪስ እና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ ገለጸ፡፡

ቢሮው በአጋርነት አብረውት ከሚሰሩ ተቋማት ጋር በ2017 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ስድስት ወራት በቅንጅት የተሰሩ ስራዎች አፈጻጸምን ገምግሟል፡፡

በግምገማ መድረኩ ላይ አዲስ ሚዲያ ኔትወርክ በቴሌቪዥን እና በኤፍ ኤም 96.3 ሬዲዮ በሚያቀርባቸው አገልጋይ በተሰኙ ፕሮግራሞቹ ላበረከተው የላቀ አስተዋፅዖ የእውቅና እና የምስጋና ምስክር ወረቀት ተበርክቶለታል፡፡

በመድረኩ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የፐብሊክ ሰርቪስ እና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ ሃላፊ ጀማሉ ጀንበር (ዶ/ር) በአገልግሎት አሰጣጡ ላይ ያሉ ችግሮች እንዲፈቱ የአዲስ ሚዲያ ኔትወርክ ሚና የጎላ እንደነበር ገልጸዋል፡፡

ቢሮው በቀጣይም የህዝቡን ጥያቄና ፍላጎት ተደራሽ ለማድረግ ከኤ ኤም ኤን ጋር የበለጠ ተቀራርቦ እንደሚሰራ አረጋግጠዋል፡፡

አዲስ ሚዲያ ኔትወርክ በሬዲዮ እና በቴልቪዥን በሚተላለፉ አገልጋይ በተሰኙ ፕሮግራሞቹ በአገልግሎት አሰጣጡ ላይ የሚነሱ ችግሮችን ነቅሶ በማሳየቱ የማስተካከያ እርምጃ እንዲወሰድ ማስቻሉን ቢሮው ያስጠናው ጥናት ማመላከቱም ተገልጿል፡፡

የአዲስ አበባ ፐብሊክ ሰርቪስ እና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ፣ አዲስ ሚዲያ ኔትወርክን ጨምሮ ከ14 አጋር ተቋማት ጋር በጋራ እየሰራ እንደሚገኝ ተገልጿል፡፡

በነፃነት ጀማል

All reactions:

89You, Lachiisaa Caalumaa and 87 others

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review