AMN – መጋቢት 6/2017 ዓ.ም
አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ለብልፅግና ፓርቲ 5ኛ ዓመት የምስረታ በዓል እና 2ኛ ጠቅላላ ጉባዔ መሳካት ላበረከተው አስተዋፅዖ ዕውቅና ተሰጠው፡፡
ለብልፅግና ፓርቲ 5ኛ ዓመት የምስረታ በዓል እና 2ኛ ጠቅላላ ጉባዔ በስኬት መከናወን አስተዋፅኦ ላበረከቱ አካላት የዕውቅና መርሐ-ግብር በመካሄድ ላይ ይገኛል።
በመርሐ-ግብሩ የብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አደም ፋራህን ጨምሮ የፓርቲው ከፍተኛ አመራሮች፣ ባለሀብቶች፣ የተቋማት ኃላፊዎች እና የሚዲያ ተቋማት ተገኝተዋል።
አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ለብልፅግና ፓርቲ 5ኛ ዓመት የምስረታ በዓል እና 2ኛ ጠቅላላ ጉባዔ መሳካት ላበረከተው አስተዋፅዖ የተሰጠውን ዕውቅና እና የምስክር ወረቀት የአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ካሳሁን ጎንፋ ተቀብለዋል፡፡
አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ በከተማ እና በሀገር አቀፍ ደረጃ የሚከናወኑ የተለያዩ ሁነቶችን በቀጥታ ሽፋን በመስጠት እያበረክተ ላለው አስተዋፅዖ ዕውቅና ማግኘቱን ቀጥሏል፡፡

የሁለቱን ምክር ቤቶች ጉባኤዎች፣ የብልጽግና ፓርቲ ጉባኤ፣ የብሔሮች ብሔረሰቦች እና ህዝቦች ቀን በዓል፣ የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት ጉባኤዎች እና ሌሎች በርካታ ሁነቶችን ለውድ አድማጭ ተመልካቾቹ በስኬት እና በጥራት በማድረስ ላበረከተው አስተዋፅዖም ዕውቅና ማግኘቱ ይታወቃል፡፡