አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ በብሔሮች’ ብሔረሰቦች እና ህዝቦች በአል በሰራቸዉ አብሮነትን የሚያጎሉ እና ኢትዮጵያዊነትን የሚያንፀባርቁ ስራዎቹ ከአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት እዉቅና እና ምስጋና አገኘ

You are currently viewing አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ በብሔሮች’ ብሔረሰቦች እና ህዝቦች በአል በሰራቸዉ አብሮነትን የሚያጎሉ እና ኢትዮጵያዊነትን የሚያንፀባርቁ ስራዎቹ ከአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት እዉቅና እና ምስጋና አገኘ

AMN – ታኅሣሥ 13/2017 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት በብሔሮች’ ብሔረሰቦች እና ህዝቦች በአል ላይ ጉልህ አስተዋፅኦን ለተወጡ ተቋማት እዉቅና እና ምስጋና ሰጥቷል፡፡

በዚህ መርሀ ግብር ላይ እዉቅና ካገኙ ተቋማት መካከል አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ አንዱ ነዉ፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ በተለያዩ መርሀ ግብሮች የተከበረዉን የብሔሮች’ ብሔረሰቦች እና ህዝቦች በአል ወደ ተመልካቾቹ ‘አድማጮቹ እና አንባቢዎቹ በብቃት እና በትጋት ወደ ህዝብ ሲያደርስ የነበረዉ አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ በደቡብ ኢትዮጽያ ክልል አርባ ምንጭ ከተማ በመገኘት ትልቅ አሻራዉን አስቀምጧል፡፡

በምክር ቤቱ ያገኘውን እዉቅና እና ምስጋና የአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ካሳሁን ጎንፋ ከአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት ዋና አፈጉባኤ ወይዘሮ ቡዜና አልከድር እጅ ተቀብለዋል፡፡

በተመስገን ይመር

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review