አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ በኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (INSA) ያስገነባውን አዲስ ዌብ ፖርታል በዛሬው ዕለት በይፋ ስራ አስጀመረ

You are currently viewing አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ በኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (INSA) ያስገነባውን አዲስ ዌብ ፖርታል በዛሬው ዕለት በይፋ ስራ አስጀመረ

AMN-ታህሣሥ 24/2017 ዓ.ም

ዌብ ፖርታሉ በራሱ ተደራሽ ከሚያደርጋቸው ይዘቶች በተጨማሪ የቴሌቪዤን፣ ሬዲዮና የኤኤምኤን ፕላስ (AMN-ፕላስ) የ24 ሰዓት ስርጭቶችን በቀጥታ ተደራሽ ማድረግ የሚያስችል ነው። በተጨማሪም የአዲስ ልሳን ጋዜጣን ይዘቶች ተደራሽ ያደርጋል።

የትውልዱ ድምፅ የመሆን አላማ ያላቸው ተዓማኒ መረጃዎችን በሁሉም የሚዲያ አግባቦች ለመላው ዓለም ተደራሽ እያደረገ የሚገኘው ኤ ኤም ኤን የስርጭት አድማሱን ከፍ ለማድረግ አዲሱ ዌብ ፖርታል ከፍተኛ ሚና እንደሚኖረው የተቋሙ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ካሳሁን ጎንፋ በመርሃ ግብሩ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት ተናግረዋል።

ኤ ኤም ኤን በዲጂታል ሚዲያው ዘርፍ ለሚያክናውናቸው ተግባራት ሃላፊነቱን በአግባቡ ይወጣ ዘንድ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ የተቋሙ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ዮዳሄ አርዓያስላሴ ተናግረዋል።

አዲሱ ዌብ ፖርታል ለበይነመረብ ጥቃት ፣ ለኮምፒውተር ቫይረስ እና ለመረጃ መንታፊዎች እንዳይጋለጥ አስፈላጊ የደህንነት መስፈርቶች እንዲሟሉለት ተደርጓልም ነው የተባለው።

በ7 ቋንቋዎች አገልግሎት የሚሰጠው ድረ-ገጹ በኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር የለማ ሲሆን መረጃን በፍጥነት፣ በጥራትና በአስተማማኝ ደህንነት ተደራሽ ለማድረግ ያግዛል ነው የተባለው።

የኤኤም ኤን ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ካሳሁን ጎንፋ የተመረቀውን ፖርታል ከኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ዮዳሄ አርዓያስላሴ ተረክበዋል።

በካሳሁን አንዱዓለም

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review