AMN – ታኅሣሥ 29/2017 ዓ.ም
አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ የገና በዓልን በጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል እያሳለፉ ለሚገኙ ታካሚዎችና አስታማሚዎች የምሳ ግብዣ መርሃግብር አካሂዷል።
ኤ ኤም ኤን በሆስፒታሉ የሚገኙ ታካሚዎች እና አስታማሚዎች ከቤተሰብ በመራቃቸው ምክንያ ብቸኝነት እንዳይሰማቸው እበማሰብ ነው ይህን ፕሮግራም ያዘጋጀው ።
የኤ ኤም ኤን ቴሌቪዥን ዜናና ወቅታዊ ዲቪዥን ሀላፊ አቶ ገመቺስ ምህረቴ እንዳሉት ሚዲያው መረጃዎችን ተደራሽ ከማድረግ ጎን ለጎን የተለያዩ የሰው ተኮር ስራዎች እና ማህበራዊ ሀላፊነት ላይ የበኩሉን እየተወጣ መሆኑን ጠቅሰዋል።
በቀጣይም መሰል ተግበራቶች ተጠናክሮ ይቀጥላሉ ብለዋል።
የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የጤና ሳይንስ ኮሌጅ ቺፍ ኤክስኩቲቭ ዳይሬክተር ፕሮፌሰር አንዷለም ደነቀ በበኩላቸው በአልን ታካሚዎችን በመጎብኘትና የምሳ መርሃ ግብር በማካሄዱ ኤ ኤም ኤንን አመስግነዉ ሌሎችም መሰል ተግባራቶች ላይ እንዲሳተፉ ጥሪ አስተላልፈዋል።
በመርሃ ግብሩ ላይ የኤ ኤም ኤን እና የሆስፒታሉ ሀላፊዎች እና ሰራተቾች ተሳትፈዋል።
በአልማዝ ሙሉጌታ