AMN- መስከረም 30/2017 ዓ.ም
የአዲስ አበባ የሀይማኖት ተቋማት ጉባኤ 12ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤውን እያካሄደ ነው፡፡
በመድረኩ ላይ የ2017 በጀት ዓመት ዕቅድን በተሻለ ሁኔታ ለመፈጸምና ይበልጥ ኢትዮጵያዊ አንድነት እንዲጠናከርና በሀይማኖት ተቋማት መካከል ያለዉ ግንኙነት እንዲጎለብት ባለድርሻ አካላት ሃላፊነታቸውን በትጋትና በቅንነት እንዲወጡም ጥሪ ቀርቧል።
የአዲስ አበባ የሀይማኖት ተቋማት ጉባኤ ተልዕኮ እንዲሳካ እገዛ ላደረጉ ባለድርሻ እና ተባባሪ አካላትም እውቅና ሠጥቷል::
አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ከአዲስ አበባ የሀይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጋር በጋራ በመስራት ለተወጣው ማህበራዊ ኃላፊነት እውቅና ተሰጥቶታል ::
አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ሀይማኖታዊ በዓላት ሲከበሩ ሙሉ ሽፋን በመስጠት በተለይም ሀይማኖቶች ለአገር ሰላም፣ ለህዝቦች አብሮነትና ወንድማማችነት አርዓያ መሆናቸውን በማጉላት በኩል እና ምዕመናንን በማስተማር ግንዛቤ እንዲያገኙ በማድረግ በኩል ላበረከተው አስተዋጽኦ ነው እውቅናው የተሰጠው ::
በአንዋር አህመድ