አዲስ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳትን ለመምረጥ የሚካሄደው ጉባኤ በግንቦት እንደሚጀመር ቫቲካን አስታወቀች

You are currently viewing አዲስ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳትን ለመምረጥ የሚካሄደው ጉባኤ በግንቦት እንደሚጀመር ቫቲካን አስታወቀች

AMN- ሚያዚያ 20/2017 ዓ.ም

የርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራሲስ የቀብር ሥነ ሥርዓትን ተከትሎ አዲስ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳትን ለመምረጥ ጉባኤው በፈረንጆቹ ግንቦት 7 እንደሚጀመር ቫቲካን አስታውቃለች።

የካቶሊክ ቤተክርስትያን ቀጣዩን መሪ ለመምረጥ ከዓለም ዙሪያ 135 ካርዲናሎች በሲስቲን ቻፕል ይሰበሰባሉ።

ያለፉት ጉባኤዎች አጭር ጊዜን የወሰዱ ቢሆንም፣ ቀጣዩ ግን በፖፕ ፍራንሲስ የተሰየሙት አብዛኛዎቹ ካርዲናሎች ተገናኝተው ስለማያውቁ ረዘም ያለ ጊዜ ሊወስድ ይችላል መባሉን ሬውተርስ ዘግቧል።

ጉባኤዎች የሚካሄዱበት ጥንታዊው ሲስቲን ቻፕልም ለጉባኤው ዝግጅቶችን ለማድረግ ሲባል ለጎብኚዎች ዝግ እንደሚሆንም በመረጃው ተመላክቷል።

በሊያት ካሳሁን

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review