AMN- ጥቅምት 20/2017 ዓ.ም
አዲስ አበባ ቀዳሚ መዳረሻ የመሆን ግዙፉ ዐቅሟ ከጊዜ ወደ ጊዜ እውን እየሆነ ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በማህበራዊ የትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልእክት አዲስ አበባ በርካታ ሀገራዊና ዓለም አቀፋዊ ኹነቶችን በማስተናገድ የቆየች ከተማ ናት ብለዋል፡፡
ቀዳሚ መዳረሻ የመሆን ግዙፉ ዐቅሟ ከጊዜ ወደ ጊዜ እውን እየሆነ ነው ሲሉም ገልጸዋል።
ለነዋሪዎች ምቹ ከተማ ለመሆን በምታደርገው ጉዞ ብቻ ሳይሆን እንዲሁም በእንግዳ ተቀባይነቷም የላቀች እንድትሆን፣ ከፍተኛ ጥራት ያለው የአገልግሎት አሰጣጥን፣ ደኅንነትን እና የመዲናችንን የበለጸገ ታሪክ የሚያከብር የቱሪዝም አቅርቦትን ለማዳበር በሁሉም ባለድርሻ አካላት መካከል የተቀናጀ ጥረት ወሳኝ ነው ሲሉም አመልክተዋል፡፡