አዲስ አበባ በተማሪዎች እና በአቅመ ደካሞች ምገባ ተምሳሌት የሆኑ ስራዎችን እየሰራች ነው፡- አቶ ጃንጥራር አባይ

You are currently viewing አዲስ አበባ በተማሪዎች እና በአቅመ ደካሞች ምገባ ተምሳሌት የሆኑ ስራዎችን እየሰራች ነው፡- አቶ ጃንጥራር አባይ

AMN- መስከረም 30/2017 ዓ.ም

አዲስ አበባ በተማሪዎች እና በአቅመ ደካሞች ምገባ ተምሳሌት የሆኑ ስራዎችን እየሰራች መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ እና የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ጃንጥራር አባይ ገለጹ፡፡

ለ2 ቀናት የሚቆየው 6ተኛው ቀጠናዊ የMilan Urban Food Policy Pact Forum በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው።

ፎረሙ “የትምህርት ቤቶች ምገባ ለጤናማ እና ዘላቂነት ላለው የአፍሪካ ከተሞች” በሚል መሪ ሀሳብ ነው እየተካሄደ ያለው።

በመድረኩ አቶ ጃንጥራር አባይን ጨምሮ በኢትዮጵያ የጣሊያን አምባሳደር አጎስቲኖ ፓሌሲ፣ከተለያዩ የአፍሪካ ከተሞች የተወጣጡ አመራሮች እና ባለድርሻ አካላት እየተሳተፉ ይገኛሉ።

አሁን ላይ ከተማ አስተዳደሩ ከ800 ሺ በላይ ተማሪዎችን እየመገበ መሆኑን እና የምገባ ማዕከላት ቁጥርንም 21 ማድረሱን አቶ ጃንጥራር አመልክተዋል፡፡

በኢትዮጵያ የጣሊያን አምባሳደር አጎስቲኖ ፓሌሲ ፕሮግራሙ ጤናማ ትውልድ ለመፍጠር ያለውን የላቀ አበርክቶ ጠቁመው የጣሊያን መንግስት ዘርፉን መደገፍ አጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።

አዲስ አበባ በትምህርት ቤቶች የምገባ ፕሮግራም’ ምርጥ ተሞክሮ የ8ኛው የMilan Urban Food Policy Pact global Forum ዘላቂ አመጋገብ እና ሥነ-ምግብ ዘርፍ በዓለም አቀፍ ደረጃ የሽልማት አሸናፊ የሆነች ሲሆን ይህም ፎረሙን ለማዘጋጀት ተመራጭ እንዳደረጋት ተገልጿል።

በሀብታሙ ሙለታ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review