አዲስ አበባ በዓለምአቀፍ ደረጃ ተመራጭ የትምህርት መዳረሻ እንድትሆን በትኩረት እየተሰራ ነው – አቶ አደም ኑሪ

You are currently viewing አዲስ አበባ በዓለምአቀፍ ደረጃ ተመራጭ የትምህርት መዳረሻ እንድትሆን በትኩረት እየተሰራ ነው – አቶ አደም ኑሪ

AMN- ሚያዝያ 6/2017 ዓ.ም

አዲስ አበባ ከተማን የትምህርት፣ የምርምር እና በዓለም አቀፍ ደረጃ ተመራጭ የትምህርት መዳረሻ እንድትሆን ለማስቻል በኮሪደር ልማቱ በትኩረት እየተሰራ ይገኛል ሲሉ አቶ አደም ኑሪ ገለጹ፡፡

አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፕላንና ልማት ቢሮ፣ በከተማዋ ሊገነባ ስለታሰበዉ የዩኒቨርሲቲ መንደር ፕሮጀክት ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል።

አዲስ አበባ ከተማን የብልጽግና ተምሳሌት ለማድረግ ያስችላል ተብሎ ወደ ተግባር የተገባው የዩኒቨርሲቲ መንደር ግንባታ፣ ከተማዋ በ2027 ግንባር ቀደም የትምህርት፣ የምርምር እና በሌሎች መስኮች ተመራጭ መዳረሻ እንድትሆን ለማስቻል ራዕይን የያዘ ነው ብለዋል።

የዩኒቨረሲቲ መንደሩ ግንባታ ከቅደመ መደበኛ እስከ ከፍተኛ የትምህርት እና የምርምር ተቋማት፣ቤተ እምነቶች፣ የወንዝ ዳርቻ ልማቶች፣ የንግድ እና የቱሪዝም መዳረሻዎች በማካተት ለመገንባት የታቀደ መሆኑንም ገልጸዋል።

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ መምህር ኢሳያስ ገብረዮሀንስ (ዶ/ር) በበኩላቸው፣ የተያዘዉን እቅድ ስኬታማ ለማድረግ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በጋራ እየሰራ መሆኑን አስታውቀዋል።

እንዲሁም የትምህርት ሚኒስቴርን ጨምሮ ሌሎች ባለድርሻ አካላትም በጋራ እየሰሩ መሆናቸው ተመላክቷል።

በሩዝሊን መሐመድ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review