አዲስ አበባ ባለፉት አመታት የኪነ ጥበቡ ዘርፍ ትውልዱን በማነቃቃት ለፈጠራ የሚተጋ እንዲሆን ለማስቻል ውጤታማ ስራ መስራቷን የከተማ ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ ተናገሩ

You are currently viewing አዲስ አበባ ባለፉት አመታት የኪነ ጥበቡ ዘርፍ ትውልዱን በማነቃቃት ለፈጠራ የሚተጋ እንዲሆን ለማስቻል ውጤታማ ስራ መስራቷን የከተማ ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ ተናገሩ

AMN ግንቦት 30/2017

ከንቲባዋ ይህንን ያሉት ከኪነ ጥበብ ባለሞያዎች ጋር ሀገር እና ጥበብ ለኢትዮጵያ ማንሰራራት በሚል በተዘጋጀ የውይይት መድረክ ላይ ነው።

ኢትዮጵያ ብሎም መዲናችን አዲስ አበባ ባለፉት ጥቂት አመታት እጅግ አመርቂ የልማት ስራዎችን መከወኗን የጠቀሱት ከንቲባ አዳነች ከተማዋ እንድትዘምን እና ለዜጎችም ምቹ እንድትሆን ዘርፈ ብዙ ስራዎች ተሰርተዋል ነው ያሉት።

በታሪክ እና ትውልድ ግንባታ ረገድም ትልቅ ስራ ስለመሰራቱም ጭምር ጠቅሰዋል።

አዲስ አበባ በአፍሪካ ምርጧ እና ምቹ ህጻናት በአዕምሮ እና ስነ ልቦና ተኮትኩተው የሚያድጉባት እንድትሆን ከስረ መሰረቱ እየሰራች መሆኑን የጠቀሱት ከንቲባዋ ፤የኪነ ጥበብ ዘርፉ በሀገረ መንግስት ግንባታ እና የልማት ስራዎች ውስጥ ሊኖረው የሚችለውን ሚና በመረዳትም እየተሰራ መሆኑን ጠቅሰዋል።

ከነዚህ መካከል ግንባታው ተጓቶ የነበረው የአዲስ አበባ ህጻናትና ወጣቶች ትያትር ቤት ግንባታ እንዲፋጠን በማድረግ በቅርቡ ወደ አገልግሎት እንዲገባ እየተሰራ መሆኑን እና ሌሎችም ቁጥራቸው የበዙ የከተማዋ ትያትር ቤቶች የማደስ ተግባሩ የዚሁ አካል መሆኑንም ጠቅሰዋል።

የኪነ ጥበብ ዘርፍ በሀገር ግንባታ ላይ ያለው ሚና ትልቅ በመሆኑም የዛሬው ትውልድ የሰራቸው እንደ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ፤የአረንጓዴ አሻራ ልማት እና ሌሎችንም አሁንም በዚህ ሙያ ማጉላት ይጠበቅብናል ብለዋል።

ዘርፉ ሀገርን ለመለወጥ እና ዜጋን ለማትጋት ያለው ሚና ትልቅ በመሆኑ አብረን እንስራ ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል።

በመድረኩ የተገኙት የኪነ ጥበብ ባለሞያዎችም አዲስ አበባ በየጊዜው ራሷን እያደሰች ያለችበት ሁኔታ አስገራሚ መሆኑን ጠቅሰዋል።

እንደ የለነገዋ የሴቶች የተሃዲሶ እና ክህሎት ማበልጸጊያ ማዕከል ያሉ በትውልድ ላይ የሚሰሩ ስራዎችም ተጠናክረው መቀጠል አለባቸው ነው ያሉት።

በአፈወርቅ አለሙ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review