“አዲስ ኢንተርናሽናል ኮንቬንሽን ማዕከል” ግንባታን በማጠናቀቅ ላይ እንገኛለን-ከንቲባ አዳነች አቤቤ

You are currently viewing “አዲስ ኢንተርናሽናል ኮንቬንሽን ማዕከል” ግንባታን በማጠናቀቅ ላይ እንገኛለን-ከንቲባ አዳነች አቤቤ

AMN – የካቲት 3/2017 ዓ.ም

በኢትዮጵያ የመጀመሪያ፣ ግዙፍ እና አለምአቀፍ ደረጃውን የጠበቀ “አዲስ ኢንተርናሽናል ኮንቬንሽን ማዕከል” ግንባታን በማጠናቀቅ ላይ እንገኛለን ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ።

ከንቲባዋ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባጋሩት መልዕክት፣ የኢትዮጵያን ፈጣን ለውጥ ሊገታው የሚችል ምድራዊ ሀይል የለም! ብለዋል፡፡

አምና በዚህ ወቅት የዓድዋ ድል መታሰቢያን፣ ዘንድሮ ደግሞ በሀገሪቱ የመጀመሪያ፣ ግዙፍ እና አለምአቀፍ ደረጃውን የጠበቀ “አዲስ ኢንተርናሽናል ኮንቬንሽን ማዕከል” ግንባታን በማጠናቀቅ ላይ እንገኛለን ሲሉም ገልጸዋል።

ይህ አለምአቀፍ ደረጃውን የጠበቀ የኮንቬንሽን እና የኤግዚቢሽን ማዕከል ትላልቅ አህጉር አቀፍ እና አለምአቀፍ ኹነቶችን ለማስተናገድ በሚያስችል ደረጃ በመጠናቀቅ ላይ መሆኑን መገምገማቸውን ከንቲባ አዳነች አስታውቀዋል::

“ቀሪ ውስን ስራዎችንም በፍጥነት እና በጥራት ለማጠናቀቅ ተግተን በመስራት ላይ እንገኛለን” ብለዋል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review