አገራዊ የቡና ኢግዚቢሽን እና የእውቅና መድረክ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት እየተካሄደ ነው

You are currently viewing አገራዊ የቡና ኢግዚቢሽን እና የእውቅና መድረክ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት እየተካሄደ ነው

AMN- መስከረም 30/2017 ዓ.ም

መድረኩ በቡና ዘርፍ ምርት እና ምርታማነትን በማሳደግ ረገድ ለተገኙ ስኬቶች እውቅና የሚሰጥበት ነው ።

የግብርና ሚንስትሩ ግርማ አመንቴ (ዶ/ር) እንደገለጹት በኢትዮጵያ የቡና ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ በተሰራው ስራ በ2016 በጀት ዓመት በኢትዮጵያ ኤክስፖርት ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ 1 ነጥብ 43 ቢሊዮን የአሜሪካን ደላር ማግኘት መቻሉን አመልክተዋል።

የ2016 በጀት ዓመት የሐምሌና የነሃሴ ወራት አፈጻጸም 82ሺ 853 ቶን ቡና በመላክ 377 ሚሊዮን የአሜሪካ ደላር ተገኝቷል ተብሏል ።

ይህም ከ2015 በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር በገቢ 41 በመቶ ጭማሪ የታየበት መሆኑ ተጠቁሟል።

በመድረኩ ላይ ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ጨምሮ የፌደሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አገኝሁ ተሻገር፣ የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት ሽመልስ አብዲሳ፣ሌሎች የመንግስት ከፍተኛ ባለስልጣናት እና ቡና አምራችና ላኪዎች ታድመውበታል።

በፋሲል ጌታቸው

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review