AMN-መስከረም 21/2017 ዓ.ም
”ክብርና ፍቅር ለአረጋውያን” በሚል መሪ ሀሳብ አገር አቀፍ የአረጋውያን ቀን ዛሬ በጋምቤላ ከተማ እየተከበረ ነው።
በአረጋውያን ቀን አከባበር ላይ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ሂክማ ከይረዲንና በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የጋምቤላ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አለሚቱ ኡሞድን ጨምሮ የፌዴራልና የክልል የአመራር አካላት እንዲሁም እንግዶች ተገኝተዋል።
በመርሃ ግብሩ ላይ በኢትዮጵያ አረጋውያንና ጡረተኞች ብሔራዊ ማህበር፣ በኢትዮጵያ ጥንታዊ አርበኞች ማህበርና በኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን እለቱን የሚዘክሩ መልዕክቶች ይቀርባሉ ተብሎ ይጠበቃል።
በተጨማሪም በትውልድ ቅብብሎሽ የአረጋውያን የልምድ ማጋራትና በእግር ጉዞ በዓሉ ተከብሮ እንደሚውል የድርጊት መርሃ ግብሩ ያመላክታል።
በዓሉ በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ34 ጊዜ፤ በኢትዮጵያ ደግሞ ለ33ኛ ጊዜ እየተከበረ እንደሚገኝ ኢዜአ ዘግቧል።
መድረኩ የክልሉ ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ከኢ.ፌ.ዴ.ሪ ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ጋር በመተባበር የተዘጋጀ ነው።