AMN – ታኅሣሥ 28/2017 ዓ.ም
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባዔ ታገሰ ጫፎ በአቶ ቡልቻ ደመቅሳ ሕልፈት የተሰማቸውን ሃዘን ገልጸዋል፡፡
አቶ ታገሰ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልእክት በቀድሞ የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት አባል አቶ ቡልቻ ደመቅሳ ሕልፈተ ሕይወት የተሰማኝን ሃዘን እገልጻለሁ ብለዋል፡፡
አቶ ቡልቻ በኢትዮጵያ ፖለቲካ፣ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚ መስክ ላበረከቱት አስተዋጽኦ ምስጋና አቅርበዋል፡፡
ለቤተሰቦቻቸው እንዲሁም ለወዳጅ ዘመዶቻቸውም መጽናናትን ተመኝተዋል፡፡