አፍሪካዊቷ እንስት የዓለም የንግድ ድርጅትን ለመምራት በድጋሚ ተመረጡ

You are currently viewing አፍሪካዊቷ እንስት የዓለም የንግድ ድርጅትን ለመምራት በድጋሚ ተመረጡ
  • Post category:ዓለም

AMN ህዳር 20/2017 ዓ.ም

ብቸኛዋ ሴት አፍሪካዊት የዓለም የንግድ ድርጅትን ለመምራት በድጋሚ ተመርጠዋል፡፡

ላለፉት አራት ዓመታት የዓለም የንግድ ድርጅትን የመሩት አፍሪካዊቷ ንጎዚ ኦኮንጆ (ዶ/ር) በድጋሚ ድርጅቱን እንዲመሩ በሙሉ ድምፅ ተመርጠዋል።

ለሁለት ቀናት ጠቅላላ ጉባኤውን ያካሄደው ድርጅቱ ዳይሬክተሯን በድጋሚ ለመምረጥ የቻለው ባለፉት ፈታኝ ዓመታት ምጣኔ ሃብቱ እንዲረጋጋ በሠሩት ሥራ መሆኑን ገልጿል።

ናይጀሪያዊቷ ዶክተር ንጎዚ ድርጅቱን ለቀጣይ አራት ዓመታት የሚመሩ ሲሆን፤ ድርጅቱን በመምራትም ብቸኛዋ ሴት አፍሪካዊት መሆናቸውን ተቋሙ በድረ-ገፁ ባወጣው መረጃ አመላክቷል።

በሲሳይ ንብረቱ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review