AMN-መስከረም 22/2017 ዓ.ም
እስራኤል ተጨማሪ ወታደሮችን ወደ ሊባኖስ መላኳን ተከትሎ ኢራን ለፈጸመችው ጥቃት ዋጋ ትከፍላለች ሲሉ የአስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒያሚን ኔታንያሁ አስጠንቅቀዋል ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒያሚን ኢራን ትናንት ሌሊት ወደ እስራኤል 180 የሚሆኑ ሚሳኤሎች በማስወንጨፏ ዋጋ ትከፍላለች ብለዋል፡፡
ከተወነጨፉት ሚሳኦሎች ውስጥ አብዛኞቹ ተመተው መውደቃቸውን የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ በጥቃቱ በዌስት ባንክ የአንድ ፍልስጤማዊ ህይወት ሲያልፍ፣ በማእከላዊ እስራኤል አንድ ትምህርት ቤት እና በቴላቪቭ ደግሞ ሆቴል መመታታቸውን ተናግረዋል፡፡
ኢራን እርምጃውን የሂዝቦላህ መሪ ሀሰን ናስረላ መገደልን ጨምሮ እስራኤል እየፈፀመች ላለው ጠብ አጫሪ ድርጊቶች ምላሽ ነው ማለቷን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡
እስራኤል በዚህ ሳምንት መጀመሪያ ላይ አካሂዳለሁ ላለችው ዘመቻ ተጨማሪ እግረኛ ኃይሎችን ወደ ሊባኖስ እየላከች መሆኗን ተከትሎ ነዋሪዎች መንደሮችን ለቀው እንዲወጡ ተነግሯቸዋል ተብሏል።
ሂዝቦላህ በበኩሉ በሊባኖስ የእስራኤል እግረኛ ጦር ሊፈጽም ለሞከረው ጥቃት የአጸፋ ምላሽ መስጠቱንና አሁንም ሮኬት መተኮሱን እንደቀጠለ አመላክቷል፡፡