ኢሬቻ ባህላዊ እሴቱን ጠብቆ አንድነትን በሚያጠናክር መልኩ ሊከበር ይገባል፡- አቶ አለማየሁ እጅጉ

You are currently viewing ኢሬቻ ባህላዊ እሴቱን ጠብቆ አንድነትን በሚያጠናክር መልኩ ሊከበር ይገባል፡- አቶ አለማየሁ እጅጉ

AMN-መስከረም 21/2017 ዓ.ም

ኢሬቻ ባህላዊ እሴቱን ጠብቆ አንድነትን በሚያጠናክር መልኩ ሊከበር እንደሚገባ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ምክትል ሀላፊና የፖለቲካ ዘርፍ ሀላፊ አቶ አለማየሁ እጅጉ ገለፁ።

መስከረም 25 እና 26 ቀን 2017 ዓ.ም በአዲስ አበባ በሆራ ፊንፊኔ እና በቢሾፍቱ የሆራ አርሰዴ የሚከበረውን የኢሬቻ በዓል አስመልክቶ የአዲስ አበባ ከተማ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ አዘጋጅነት ከ11ዱ ክፍለ ከተማ የተወጣጡ ወጣቶች እና ከሸገር ከተማ አስተዳደር የተወጣጡ ወጣቶች ውይይት እያደረጉ ይገኛል።

በመርሃ ግብሩ ላይ የተገኙት አቶ አለማየሁ እጅጉ እንደገለፁት በዓሉ ሁሉም ህብረተሰብ ያለምንም የሃይማኖት የፖለቲካ ና የእድሜ ልዩነት በጋራ የሚያከብረው ነው።

የአዲስ አበባ ወጣቶች እና የሸገር ከተማ ወጣቶች ለበዓሉ ወደ ከተማዋ የሚገቡ እንግዶችን በመቀበል የተለመደ ሚናቸውን እንዲወጡም ጥሪ አቅርበዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ሀላፊ አቶ በላይ ደጀን በበኩላቸው የኢሬቻ በዓል የእርቅ የሰላምና የአንድነት መሆኑና አሁን ላይ የኢሬቻ በዓል ከኢትዮጵያ አልፎ የዓለም ሃብት በመሆኑ በዓሉ በተሳካ መልኩ ሊከበር እንደሚገባ አመለክተዋል።

በመሀመድ ኑር አሊ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review