AMN- መስከረም 22/2017 ዓ.ም
የአራዳ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የኢሬቻ በዓል አከባበር እና በበዓሉ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ ላይ ከተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎች ጋር ዉይይት እያካሄደ ነው።
በውይይቱ ላይ ኢሬቻ የሰላም ፣ የአብሮነት ፣ የአንድነት ፣ የፍቅር እና የይቅርታ በዓል ሆኖ እንዲከበር ክፍለ ከተማው ከተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎች ጋር ውይይት እየተካሄደ ነው።
ኢሬቻ እና ሰላም የማይነጣጠሉ መሆናቸው በውይይ ላይ የተነሳ ሲሆን ኢሬቻ ለሰላም ልዩ ቦታ እንዳለው ተጠቁሟል፡፡
በዓሉ ሰላም የሚለምንበት እና ፈጣሪ የሚመሰገንበት እንደሆነም ተነስቷል፡፡
በዓሉ የሕዝቦችን አንድነት እና አብሮነት የሚያጎለብት እና የኦሮሞ ሕዝብ ከሌሎች ሕዝቦች ጋር በጋራ የሚያከብረው በዓል እንደሆነም ተጠቅሷል፡፡
በዳንኤል መላኩ