AMN – መስከረም 23/2017 ዓ.ም
ኢሬቻ በኦሮሞ ባህል የምስጋና ብቻ ሳይሆን ሠላም ፍቅርና ስለ አንድነት የሚሠበክበት በአል መሆኑን በአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ ማሾ ኦላና ገለጹ፡፡
የ2017 ዓመተ ምህረት የኢሬቻ አከባበር የማጠቃለያ መርሃ ግብር በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ተካሄዷል።
በመርሃ ግብሩ ላይ ንግግር ያደረጉት የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ሙባረክ ከማል ኢሬቻ ለኢትዮጵያውያን ትልቅ ድል ይዞ የመጣ ነው ብለዋል።
በተለይም በዓሉ በቂርቆስ ክፍለከተማ መከበር ከጀመረበት ጊዜ ወዲህ የባህል ትስስር የኢኮኖሚ ዕድገትና አንድነት የነገሰበት ሆኗል ብለዋል።
የበዓሉ አስተናጋጅ የሆነው ክፍለ ከተማው ዝግጅቱን አጠናቆ እንግዶቹን እየተጠባበቀ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡
በአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ ማሾ ኦላና በበኩላቸው፣ ኢሬቻ በኦሮሞ ባህል የምስጋና ብቻ ሳይሆን ፍቅር ሠላምና አንድነት የሚሠበክበት መሆኑን ገልጸዋል።
በምትኩ ተሾመ