AMN – መስከረም 21/2017 ዓ.ም
ኢሬቻ የሰላም እና የአንድነት ተምሳሌት ሆኖ እንዲቀጥል የድርሻቸውን እንደሚወጡ ወጣቶች ገለፁ።
“ኢሬቻ የሰላም እና የአንድነት ተምሳሌት ነው” በሚል መሪ ሀሳብ የኢትዮጵያ ሰላም ልማትና ብልጽግና ድርጅት ከተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎች እና አባላቱ ጋር ውይይት አካሄዷል።
የኢትዮጵያ ሰላም ልማትና ብልጽግና ድርጅት ፕሬዝዳንት አብዱ አማን እንደገለጹት፣ ኢሬቻ የሰላም እና የአንድነት ተምሳሌት በዓል በመሆኑ እሴቱን ጠብቆ እንዲከበር ከመላ ኢትዮጵያውያን ወንድሞች ጋር በጋራ ለማክበር ድርጅቱ ተዘጋጅቷል።
የኢትዮጵያ ሰላም ልማትና ብልጽግና ድርጅት ከ3 ወራት በፊት ከሁሉም ክልሎች በተወጣጡ ወጣቶች የተመሰረተ እና ከ 1 ነጥብ 2 ሚሊዮን በላይ አባላት እንዳሉት ተገልጿል።
ድርጅቱ በአዲስ አበባ ከተማ ፣ በኦሮሚያ ፣ በአማራ እና በትግራይ ክልሎች ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት የከፈተ ሲሆን በሌሎች ክልሎች ለመክፈት ቅድመ ዝግጅት መደረጉን ፕሬዝዳንቱ ገልጸዋል።
በመንግሥት ሊሸፈኑ የማይችሉት ማህበራዊ ፣ ኢኮኖሚያዊ እና የሰላም ጉዳይ ላይ የሚሰራ ደርጅት መሆኑም ተነግሯል።
በዳንኤል መላኩ