ኢሬቻ የሰላም ፣ የእርቅ እና የወንድማማችነት ተምሳሌት ነዉ፡- የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት

You are currently viewing ኢሬቻ የሰላም ፣ የእርቅ እና የወንድማማችነት ተምሳሌት ነዉ፡- የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት

AMN- መስከረም 24/2017 ዓ.ም

ኢሬቻ የሰላም ፣ የእርቅ እና የወንድማማችነት ተምሳሌት ነዉ ሲል የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ገለጸ፡፡

የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ለኢሬቻ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት አስተላልፏል፡፡

አገልግሎቱ በመልእክቱ ኢሬቻ የኦሮሞ ህዝብ ባህላዊ ፣ ታሪካዊ እና ስነ-ልቦናዊ ዉቅር የጥንካሬ ምንጭ ነዉ ሲል አመልክቷል።

ኢሬቻ የገዳ ስርዓት እሴት ነዉ ያለው አገልግሎቱ ኢሬቻ የምስጋና ፣ የፍቅርና የደስታ ተምሳሌት ነዉ ሲልም ገልጿል፡፡

ኢሬቻ የነገ ተስፋ ብሩህነት መገለጫ ነዉ ያለው አገልግሎቱ ኢሬቻ የኦሮሞ ህዝብ ብዝሃ ቀለም እና የአንድነት አርማ መገለጫ ነዉ ብሏል።

አገልግሎቱ ኢሬቻ የኢኮኖሚ እና የቱሪዝም ምንጭ ነዉ ሲልም አመልክቷል በመልእክቱ።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review