ኢሬቻ የእርቅና የወንድማማችነት ተምሳሌት ነው- የበዓሉ ተሳታፊዎች

You are currently viewing ኢሬቻ የእርቅና የወንድማማችነት ተምሳሌት ነው- የበዓሉ ተሳታፊዎች

AMN – መስከረም 23/2017 ዓ.ም

የጉለሌ ክፍለከተማ “ኢሬቻ ለባህላችን ህዳሴ” በሚል መሪ ቃል አጎራባች ከሆኑ የኦሮሚያ ክልሎች ጋር የኢሬቻ በአልን በተለያዩ ዝግጅቶች አክብሯል።

የጉለሌ ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ ወልዴ ወገሴ፣ የ2017 ዓ.ም የኢሬቻ በአልን ለማክበር የሚመጡ እንግዶችን በክብርና በወንድማማችነት በመቀበል መዘጋጀታቸውን ገልጸዋል፡፡

በበዓሉ አባገዳዎችና ሃደ ስንቄዎች የተገኙ ሲሆን የኦሮሞ ባህላዊ የምግብ አይነቶች እና አልባሳት ቀርበዋል።

ኢሬቻ የእርቅና የወንድማማችነት ተምሳሌት ነው ያሉት የበዓሉ ተሳታፊዎች በዓሉ ሲከበር ከዚህ ቀደም የነበረውን ወንድማማችነትና አንድነትን በማጠናከር ሊሆን እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡

በዝናሽ ሞዲ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review