ኢትዮጵያና ዩጋንዳ በወታደራዊዉ መስክ በጋራ ለመሥራት ተሥማሙ

AMN-ታህሳስ 5/ 2017 ዓ.ም

የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ እና የዩጋንዳ መከላከያ ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጄነራል ሙሖዚ ኬንሩጋባ በትብብር መስራት በሚችሉባቸው ወታደራዊ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት አካሂደዋል።

የሁለቱ አገራት ጠቅላይ ኢታማዦር ሹሞች በተለያዩ ወታደራዊ ጉዳዮች ዙሪያም በጋራ ለመስራት ተስማምተዋል።

ከውይይቱ በሗላ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ በሁሉም ወታደራዊ አቅሞቻችን በጋራ ለመስራት ተስማምተናል ነው ያሉት።

እንደ ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ማብራሪያ በመረጃ፣ በወታደራዊ ኢንዱስትሪ፣በስልጠና እና መሰል ወታደራዊ ጉዳዮች ዙሪያ በትብብር ለመስራት ስምምነት ደርሰዋል።

ዩጋንዳና ኢትዮጵያ ረጅም አመታትን ያስቆጠረ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት አላቸው ያሉት ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ከስደተኞች ጋር በመመሸግ ወንጀል የሚፈፅሙ አካላትንም ለመለዋወጥ ከስምምነት ላይ መደረሳቸውን ተናግረዋል።

የዩጋንዳ መከላከያ ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም

ጄነራል ሙሖዚ ኬንሩጋባ በበኩላቸው ለተደረገላቸው ደማቅ አቀባበልና የኢትዮጵያ መንግስት ኢትዮጵያን እንዲጎበኙ ስለጋበዛቸው ምስጋና አቅርበዋል።

ከኢትዮጵያ መከላከያ ጋር በተለያዩ ወታደራዊ መስኮች በትብብር የሚሰሩት ስራዎችም

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review