AMN- ሰኔ 4/2016 ዓ.ም
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ ከደቡብ አፍሪካ የዓለም አቀፍ ግንኙነት እና ትብብር ሚኒስትር ናሌዲ ፓንዶር ጋር በሁለትዮሽ እና ክልላዊ የጋራ ጉዳዮች ላይ ፍሬያማ ውይይት አድርገዋል።
ሁለቱ ሚኒስትሮች በሁለቱ ሀገራት መካከል ከወራት በፊት የተፈረመው ስትራቴጂያዊ አጋርነት ስምምነትን ተግባራዊ ማድረግ በሚቻልባቸው ሁኔታዎች ላይም ሀሳብ ተለዋውጠዋል።
ውይይቱ የተደረገው በሩሲያ እየተካሄደ ከሚገኘው የብሪክስ የውጭ ጉዳይ እና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ሚኒስትሮች ስብሰባ ጎን ለጎን መሆኑን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
ትክክለኛውን የአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ዲጂታል ሚዲያ የትስስር አውታሮችን በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑን!