AMN – ጥር 2/2017 ዓ.ም
ኢትዮጵያን በሚገባ በማወቅና ለሌላው ዓለም በማስተዋወቅ የሀገሪቱን በጎ ገጽታ መገንባት ይገባል ሲሉ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴዔታ አምባሳደር ብርቱካን አያኖ ገለጹ፡፡
በ38ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባዔ በጎ ፈቃድ አገልግሎት ለመስጠት ስልጠና የወሰዱ ካዴቶች በብሔራዊ ቤተ-መንግስት፣ አንድነት ፓርክ፣ ሳይንስ ሙዚዬም እና በወዳጅነት ፓርክ ጉብኝት አድርገዋል፡፡
አምባሳደር ብርቱካን በዚህ ወቅት÷ኢትዮጵያ የቆዩ አኩሪ ታሪካዊ ሃብቶች ያላት ሀገር መሆኗን አውስተዋል፡፡
እነዚህን ታሪኮች ጠንቅቆ በማወቅ በጎ ፈቃደኛ ካዴቶች ለኢትዮጵያ በጎ ገጽታ ግንባታ ሊጠቀሙበት ይገባል ብለዋል፡፡
በጎ ፈቃደኛ ካዴቶች በበኩላቸው ÷የጎበኟቸው ሥፍራዎች ስለ ኢትዮጵያ ታሪክና ቅርስ አዲስ ግንዛቤ እንደፈጠሩላቸው ተናግረዋል፡፡
የሀገራቸው አምባሳደር በመሆን በሚሰማሩባቸው ተልዕኮዎች የኢትዮጵያን ገጽታ እንደሚያስተዋውቁም ማረጋገጣቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡