AMN – ሐምሌ 12/2016 ዓ.ም
ኢትዮጵያን አረንጓዴ ምድር እናደርጋታለን ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ፡፡
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ የትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልእክት “የምትተክል ሀገር፣ የሚያጸና ትውልድ” በሚል መሪ ቃል የጀመርነውን የዘንድሮውን የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር ዛሬ በጫካ ፕሮጀክትም ቀጥለናል ብለዋል፡፡
የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር ከተጀመረ በኋላ የመሬት መራቆትን በመከላከል የተፈጥሮ ኃብትን መጠበቅና የደን ሽፋን እንዲጨምር አስችሏል ሲሉ ገልጸዋል፡፡
በመሆኑም ብርደ ክረምቱን ችግኞችን በመትከል ለአረንጓዴ ምድር እንበረታለን ሲሉም አክለዋል፡፡