ኢትዮጵያን ወደከፍታዋ መውሰድ የምንችለው በግብርና እና ሌሎች የልማት መስኮች የጀመርናቸውን ሥራዎች በማጠናከር ነው:-አቶ ተመስገን ጥሩነህ

AMN- ህዳር 12/2017 ዓ.ም

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ተመስገንጥሩነህ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባስተላለፉት መልእክት በሰላም ተምሳሌቷና ጎተራዋ ሙሉ በሆነችው ደጀን ወረዳ ባዩት የጤፍ ክላስተር ልማት መደነቃቸውን ገልፀዋል።

ኢትዮጵያን ወደከፍታዋ መውሰድ የምንችለው በግብርና እና ሌሎች የልማት መስኮች የጀመርናቸውን ሥራዎች በማጠናከር ነውም ብለዋል ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ።

ለዚህም እንደ ሀገር ለክላስተር ግብርና የሰጠነው ትኩረት ከፍተኛ እመርታ እያሳየ ይገኛል።

በአማራ ክልል ትርፍ አምራች ከሆኑ አካባቢዎች አንዱ በሆነው ምስራቅ ጎጃም ዞን ደጀን ወረዳ የተመለከቱት ጤፍን በክላስተር የማልማት ሥራ የሚደነቅ መሆኑን ገልፀዋል።

በዘንድሮ የመኸር እርሻ ለግብዓት አቅርቦትና ለዘመናዊ የአስተራረስ ዘዴ ከፍተኛ ትኩረት በመስጠታችን ከፍተኛ ምርት እንደሚገኝ ተዘዋውረው የተመለከቱት የሰብል ቁመና እንደሚያሳ ጠቁመዋል።

በቀጣይም ለመስኖ ልማት እና ለሰላም ትልቅ ትኩረት ሰጥተን እንሰራለንም ብለዋል አቶ ተመስገን።

ማህበረሰቡም የሰላምና የልማት አርበኝነቱን አጠናክሮ መቀጠል አለበት ያሉት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ የምስራቅ ጎጃም ዞን ህዝብ በተለይም የደጀን ወረዳና አካባቢዋ ነዋሪዎች ላሳዩን ድንቅ የጤፍ ልማትና ላደረጉልን ደማቅ አቀባበል ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review