ኢትዮጵያውያን ለሀገር ሰላም፣ እድገትና ብልጽግና በትብብር በመሥራት ክብሯ የተጠበቀ ኢትዮጵያን ለመጭው ትውልድ ማስረከብ ይገባናል – አንጋፋው አርቲስት ደበበ እሸቱ

You are currently viewing ኢትዮጵያውያን ለሀገር ሰላም፣ እድገትና ብልጽግና በትብብር በመሥራት ክብሯ የተጠበቀ ኢትዮጵያን ለመጭው ትውልድ ማስረከብ ይገባናል – አንጋፋው አርቲስት ደበበ እሸቱ

AMN – ሀምሌ 6/2016 ዓ.ም

ኢትዮጵያውያን ለሀገር ሰላም፣ እድገትና ብልጽግና በትብብር በመሥራት ክብሯና ጥቅሟ የተጠበቀ አገር ለመጭው ትውልድ ማስረከብ ይገባናል ሲሉ አንጋፋው የጥበብ ሰው አርቲስት ደበበ እሸቱ ተናገሩ።

ትውልዱ ኢትዮጵያ ከተመጽዋችነት በመውጣት ሌሎችን የምትረዳ አገር እንድትሆን መትጋት እንደሚገባውም አስገንዝበዋል።

ከኢዜአ ጋር ቆይታ ያደረጉት አንጋፋው የጥበብ ሰው አርቲስት ደበበ እሸቱ ሀገር የሚኖረው ሁሉም ስለሀገሩ ሲያስብና ሲሰራ ነው ይላሉ።

ከመለያየት መሰባሰብ፣ ከመጠላላት መዋደድን እንዲሁም ከመገፋፋት መቀራረብን ማስቀደም እንደሚገባ አመላክተዋል።

አንዱ ለሌላው ማሰብ ካልቻለ የሀገር ፍቅር የሚገለጽበት ምንም አይነት ማሳያ እንደሌለ ጠቁመዋል።

ሀገር እንድትለማ እንድታድግና እንድትበለጽግ ሁሉም ኢትዮጵያውያን ያላቸውን በሙሉ አሟጠው ለኢትዮጵያ ሊያውሉ እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

ኢትዮጵያን የሚወድ ሁሉ ለእድገቷ ሊሰራ እንደሚገባና ከተመጽዋችነት በመውጣት ሌሎችን የምትረዳ አገር እንድትሆን መትጋት እንደሚገባ ተናግረዋል።

ኢትዮጵያውያን ለሀገር ሰላም እድገትና ብልጽግና በትብብር በመሥራት ክብሯ የተጠበቀ ኢትዮጵያን ለመጭው ትውልድ ማስረከብ እንደሚገባ ጠቁመዋል።

ትውልዱ ለኢትዮጵያ ጥቅምና ክብር በጋራ መቆም እንዳለበት አስገንዝበዋል።

ጊዜው ያመጣው ቴክኖሎጂ መልካም እድልና ተግዳሮት ይዞ መምጣቱን ገልጸው መልካም ነገሩን ለበጎ ሥራ መጠቀም ይገባል ብለዋል።

የማኅበራዊ ትስስር ገጾች መወነጃጀያ ሳይሆኑ ትውልዱን ወደ አንድነት የሚያመጡ መሆን እንዳለባቸውም ማመልከታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review