ኢትዮጵያ ለንግድና ኢንቨስትመንት መጎልበት በትኩረት እየሰራች ነው – ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር)

You are currently viewing ኢትዮጵያ ለንግድና ኢንቨስትመንት መጎልበት በትኩረት እየሰራች ነው – ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር)

AMN – መጋቢት 3/2017 ዓ.ም

ኢትዮጵያ ለንግድና ኢንቨስትመንት መጎልበት በትኩረት እየሰራች መሆኗን እና ከመቼውም ጊዜ በላይ አስቻይ ሁኔታ መኖሩን የንግድና ቀጣናዊ ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡

ሚኒስትሩ በማህበራዊ የትስስር ገፃቸው ባስተላለፉት መልዕክት፣ በኢትዮጵያ የዩናይትድ ኪንግደም ኤምባሲ የልማት ዳይሬክተር ፖል ዋልተርስ ከተመራ ቡድን ጋር በሁለቱ ሃገራት የንግድና ኢንቨስትመንት ትብብሮች ዙሪያ መወያየታቸውንም አመላክተዋል፡፡

ኢትዮጵያ እና ዩናይትድ ኪንግደም ጠንካራ የንግድ ግንኙነት ያላቸው ሀገራት መሆናቸውንም ሚኒስትሩ ገልጸዋል፡፡

ሚስተር ፓል በበኩላቸው፣ ዩናይትድ ኪንግደም ኢትዮጵያ እያሳየች ላለችው የኢኮኖሚ ሪፎርም ድጋፏን አጠናክራ እንደምትቀጥል አረጋግጠዋል፡፡

ለአለም ንግድ ድርጅት አባልነት እያደረግን ያለውን ዝግጅትም አድንቀዋል ያሉት ሚኒስትሩ፣ በሁለትዮሽ የገበያ ዕድሎች ዙሪያ በቀጣይነት በጋራ በምንሰራባቸው አግባቦች ላይ ውጤታማ ውይይት አድርገናል ብለዋል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review