AMN – የካቲት 30/2017 ዓ.ም
ኢትዮጵያ በሁሉም ዘርፍ ራሷን እንድትችል አቅደን እየሰራን ነው ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ።
በዚህም ባልጠበቅነው ፍጥነት ትግበራችን ስኬት እያመጣ ነው ብለዋል፡፡
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባጋሩት መልዕክት ፣ ሁላችንም በተሰማራንበት ዘርፍ ለሀገራችን ዕድገትና ብልፅግና እስካሁን ባገኘናቸው ስኬቶች ሳንረካ ሌት ተቀን መስራታችንን መቀጠል ይገባናል ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል።
ለእስካሁኑ ስኬቶቻችንና አስገራሚ ውጤቶች ኢትዮጵያውያን በሙሉ እንኳን ደስ አለን ሲሉም አስፍረዋል።