AMN – ጥር- 23/2017 ዓ.ም
ኢትዮጵያ በህንድ ኩምብ ሜላ ፌስቲቫል በተፈጠረ ክስተት ህይወታቸውን ላጡ ዜጎች ሀዘኗን ገለጸች።
በህንድ ፕራያጋራጅ በኩምብ ሜላ ፌስቲቫል በተፈጠረ ግርግር 15 ሰዎች ህይወታቸው ሲያልፍ በርካቶች መጎዳታቸው ይታወቃል፡፡
ይህን ተከትሎ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዛሬ ባወጣው መግለጫ ፤ በህንድ ኩምብ ሜላ ፌስቲቫል ላይ በሰዎች መብዛት ምክንያት በተፈጠረ ግርግር ህይወታቸውን ላጡ ወገኖች የተሰማውን ሀዘን ገልጿል።
የኢትዮጵያ ህዝብ እና መንግስት በዚህ ከባድ ወቅት ከህንድ ህዝብ እና መንግስት ጎን መሆኑን ገልጾ፤ ለህንድ ህዝብና መንግስት መጽናናትን ተመኝቷል።