ኢትዮጵያ በምግብ ሉዓላዊነት ከአፍሪካ 2ኛ ሆነች

You are currently viewing ኢትዮጵያ በምግብ ሉዓላዊነት ከአፍሪካ 2ኛ ሆነች

AMN- ጥቅምት 1/2017 ዓ.ም

ተቀማጭነቱን በእንግሊዝ ያደረገው አፍሪካ IOA የተሰኘ ድርጅት ባወጣው ሪፖርት ኢትዮጵያን በምግብ ራሷን የቻለች ሁለተኛዋ የአፍሪካ ሀገር መሆኗን አመልክቷል፡፡

የአፍሪካ ሀገራት ውጤታማነት እየተከታተለ ሪፖርት የሚያወጣው ድርጅቱ የተረጋጋ የፖለቲካ እና የዴሞክራሲ ስርአት እውን ያደረጉ እና ተከታታይነት ያለው የኢኮኖሚ እድገት ያስመዘገቡ አገራትን በማወዳደር ደረጃ ይሰጣል፡፡

ድርጅቱ በውጤታማነታቸው እና ባስመዘገቡት የኢኮኖሚ እድገት በደረጃ ካስቀመጣቸው 10 የአፍሪካ አገሮች ኢትዮጵያን ከደቡብ አፍሪካ በመቀጠል በምግብ ራሷን የቻለች ሁለተኛዋ አገር በማለት ደረጃውን ሰጥቷታል፡፡

ሞሮኮ፣ አልጄሪያ፣ ናይጄሪያ፣ ጋቦን፣ ርዋንዳ፣ ጋና፣ ሴኔጋል እና ናሚቢያ በቅደም ተከተል ከ3 እስከ 10 ያለውን ደረጃ መያዛቸውን ከድርጅቱ የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review