ኢትዮጵያ በሞስኮ ሩስያ እየተካሄደ ባለው የብሪክስ አባል አገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባዮች የምክክር መድረክ ላይ እየተሳተፈች ነው

You are currently viewing ኢትዮጵያ በሞስኮ ሩስያ እየተካሄደ ባለው የብሪክስ አባል አገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባዮች የምክክር መድረክ ላይ እየተሳተፈች ነው

AMN – ሐምሌ 05/2016 ዓ.ም

ኢትዮጵያ በሞስኮ ዛሬ በተጀመረው የብሪክስ አባል አገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባዮች እና የኮሚኒኬሽን ኃላፊዎች የምክክር መድረክ ላይ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ነብዩ ተድላ የተመራ ልዑክ እየተሳተፈ ነው።

አምባሳደር ነብዩ ተድላ በምክክር መድረኩ ላይ ባደረጉት ንግግር ኢትዮጵያ የብሪክስ ዓላማ በማስረፅ እና የተዛቡ መረጃዎችን በመከላከል ረገድ ከአባል አገራቱ ጋር በትብብር ለመሥራት ቁርጠኛ መሆኗን ገልፀዋል።

ቃል አቀባዩ የብሪክስን ትክክለኛ ዓላማ እና የአባል አገራቱን እኩል ተጠቃሚነት በማረጋገጥ ዙሪያ የብሪክስ አባል አገራት መገናኛ ብዙኃን በትብብር መሥራት እንዳለባቸው ተናግረዋል።

በሞስኮ የተጀመረው የምክክር መድረክ ዋና ግቡ በብሪክስ አባል አገራት መገናኛ ብዙኃን ዘንድ ተግባራዊ ትብብር እንዲጠናከር ማድረግ እና በዲጂታል ዲፕሎማሲ ሚና ዙሪያ ላይ የጋራ ውይይት ማድረግ መሆኑን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

የምክክር መድረኩ በሩስያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ማሪያ ዛካሮቫ ፕሬዝዳንትነት የሚመራ መሆኑ ተገልጿል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review