ኢትዮጵያ በተባበሩት መንግስታት አለም አቀፍ የኤሌክትሮኒክ መንግስት መለኪያ መሰረት ደረጃዋን አሻሻለች

You are currently viewing ኢትዮጵያ በተባበሩት መንግስታት አለም አቀፍ የኤሌክትሮኒክ መንግስት መለኪያ መሰረት ደረጃዋን አሻሻለች

AMN – መስከረም 8/2017 ዓ.ም

ኢትዮጵያ በተባበሩት መንግስታት አለም አቀፍ የኤሌክትሮኒክ መንግስት መለኪያ መሰረት ደረጃዋን ማሻሻሏን የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

በየሁለት አመቱ የሚወጣው የተባበሩት መንግስታት አለማቀፋዊ የኢ-መንግስት መለኪያ ትናንት በኒዮርክ ከመንግስታቱ ስብሰባ ጎን ለጎን ይፋ ሆኗል።

ይህ አለማቀፋዊ የኤሌክትሮኒክ መንግስት መለኪያ የአለም ሀገራት በየሁለት አመቱ ከሌሎች ሀገራት አንጻር እና በራሳቸው ካሳዩት እድገት ጋር በማነጻጸር ሀገራቱ በዘርፉ ያደረጉትን መሻሻሎችና ያስመዘገቧቸውን ለውጦች የሚያሳይ ነው።

በአለም አቀፍ የኤሌክትሮኒክ መንግስት ሪፖርት መሰርት ኢትዮጵያ ከነበረችበት ደረጃ በ2024 አስር ደረጃዎችን አሻሽላለች፡፡

የተባበሩት መንግስታት የኤሌክትሮኒክ መንግስት መለኪያ በሀገራቱ ያለውን ለዜጎች የሚሰጡ የኦንላይን አገልግሎቶች፣ የቴሌኮሙኒኬሽን መሰረተ ልማት እድገቶች እና የሰው ሃይል ልማት እድገቶችን በአንድ ላይ አጣምሮ የሚለካ መሆኑን የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር መረጃ ያሳያል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review