AMN – ጥር 14/2017 ዓ.ም
ኢትዮጵያ በትምህርት ዘርፍ ከህንድ ጋር ያላትን ትብብር የማስፋት ፍላጎት እንዳላት በህንድ የኢትዮጵያ አምባሳደር ፍስሃ ሻውል ገለጹ።
የህንድ የንግድ ምክር ቤት ያዘጋጀው ሁለተኛ የህንድ የትምህርት ጉባዔ በኒው ዴልሂ ተካሄዷል።
በህንድ የኢትዮጵያ አምባሳደር ፍስሃ ሻውል እና ተቀማጭነታቸውን በህንድ ያደረጉ የተለያዩ ሀገራት አምባሳደሮች በጉባዔው ላይ ተሳትፈዋል።
አምባሳደር ፍስሃ በጉባዔው ላይ ኢትዮጵያ እና ህንድ በትምህርት መስክ ያላቸውን ትብብር ማስፋት የሚችሉባቸው እድሎች እንዳሉ ገልጸዋል።
ሁለቱ ሀገራት ታሪካዊ ግንኙነት እንዳላቸው ገልጸው ትምህርት ለሀገራቱ የቆየ ወዳጅነት የማዕዘን ድንጋይ ነው ሲሉ ተናግረዋል።
አምባሳደር ፍስሃ ሀገራቱ በትምህርት እና ክህሎት ልማት ያላችውን ትብብር ማጠናከር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ከህንድ ባለስልጣናት ጋር ውይይቶችን ማድረጋቸውን በኒው ዴልሂ የኢትዮጵያ ኤምባሲ መረጃ ያመለክታል።